Contact

Mituntu Appartment B#11, Ringroad Kileleshiwa, Nairobi, Kenya

We Are Available 24/ 7. Call Now.

Read in English

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1994 ሩዋንዳ ውስጥ ዓለምን ያስለቀሰ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተፈፅሟል፡፡ በ100 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ800,000 በላይ ቱትሲ ሲቪሊያን በጭካኔ ተገድሏል፡፡ 2 ሚሊዮን ሩዋንዳውያ (ከቱትሲም ከሁቱም) ተሰደዋል፣ አብዛኛዎቹ ወደ ምስራቅ ዛየር፡፡ የዓለም ማህበረሰብ በዚህ ጭካኔ አልቅሶ ‹‹መቸም የትም እንዳይደገም›› ብሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከዛ በሃላ ብዙ የዘር ማጥፋት ጦርነቶች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተካሂደዋል፡፡

የሩዋንዳው ከተፈፀመ ከ27 ዓመት በኋላ አሁን በዚህ ጊዜ እንኳን ትግራይ ውስጥ እየተፈፀመ ነው፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት እና የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች ከክልል ኃይሎች፣ ከሶማሊያ፣ ከተባበሩት ዓረብ ኤሜሬትና ከቱርኪ ግብረ ኣበሮቻቸው ጋር በመተባበር ተጋሩን ለማጥፋት በሙሉ አቅማቸው ዘምተው በመቶ ሺ የሚቆጠር ንፁህ ህዝብ እየገደሉ፣ ሴቶች እየደፈሩ፣ ንብረት እየዘረፉ፣ መሰረተ ልማት እያወደሙ፣ ወጣቶች እጃቸው ኩርንኩሪት አስረው፣ ገድለው ወደ ገደል እና ወንዝ እየወረወሩ፣ በገጀራ እየቆራረጡ፣ እርዳታ እንዳይ ገባ እየከለከሉ ለመናገር እንኳን የሚከብድ ጭካኔ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡

ሩዋንዳ ላይ የተፈፀመው በሙሉ ትግራይ ላይ እየተፈፀመ ነው…

ከሚያመሳስሉባቸው በጣም ጥቂቶቹ፡

 • ቱትሲዎች (እንደ ተጋሩ) በተደጋጋሚ ይጠቁ ነበር
 • ተገለው መብቶቻቸው በሙሉ ተከልክለው ነበር
 • ቱትሲዎች በረሮ (#cockroache) የሚል ቅጥል ስም ተሰጥዋቸው ነበር፣ ልክ ትግራዋይ ጁንታ እንደተባለ
 • የመንግስት ወታደሮች አደንዛዥ ዕፅና አልኮል በነፃ ለማግኘት ብለው የገቡ የጎደና ተዳዳሪዎች ነበሩ – ልክ እንደ ኢትዮጵያ ወታደሮች
 • የፕሬዝዳንት ሃብያሪማና ፓርቲ ልክ እንደ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ – አብን የተደራጀው #ፋኖ#ኢንተራሃምዌ የሚባል የአደገኛ ቦዘኔዎች ስብስብ አደራጅቶ ነበር፡፡ ኢንተራሃምዌ ብዙ ጎደና አደሮች በመሰብሰብ እንዴት እንደሚዘርፉና እንደሚገድሉ በመንግስት ወታደሮች ስልጠና ተሰጣቸዋል – ልክ ፋኖ እንዲዘርፍና እንዲገድል በኢትዮጵያ ወታደሮች ሙሉ ድጋፍ እየተደረገለት እንዳለ፡፡
 • ኢንተራሃምዌ (ልክ እንደ ፋኖ) በፓርቲያቸው ባንዴራ ልክ የተሰራ ደማቅ ቀይ፣ ብጫና አረንጓዴ ቀለም ያለው ቲ-ሸርት ለብሰው ነበር፡፡
 • ኢንተራሃምዌ (ፋኖ) መንገድ በመዝጋት፣ አውቶቡሶች በማስቆም፣ መታወቅያ በመጠየቅ ቱትሲ የሆኑትን ለይተው ያጠቁ ነበር፡፡ ልክ ፋኖዎች በሕገወጥ ከ2007 ዓ/ም የግእዝ አቆጣጠር ጀምሮ ከአዲስ አበባ የአማራ ክልልን አቋርጠው ወደ ትግራይ የሚገቡ የፌደራል መንገዶች ዘግተው፣ ተጋሩ ተሳፋሪዎች ከአውቶቡስ እያሰስወረዱ በየመንገዱ እንደገደሉና እንደዘረፉ፡፡
 • ለውድቀቶቻቸውና ለአቅመቢስነታቸው ሁቱዎች በቱትሲዎች፣ አማራዎች በተጋሩ ያላክካሉ፡፡
 • ሁቱዎቹ #RTLM የሚባል ሬድዮ ነበራቸው፣ ልክ እንደ #ESAT tv (+የአማራና የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን). RTLM ፀረ-ቱትሲ መርዝ የሚተፋ ከጥላቻ ማሽን በላይ ነበር፡፡
 • የሩዋንዳ ብሔራዊ ራድዮ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ በግልፅ ያሰራጭ ነበር፡፡ ፕሮግራም መሪው አማፅያኖቹ እንደ ዱር አራዊት ጫካ ውስጥ የሚኖሩ አስፈሪዎች፣ የሰው ስጋ የሚበሉ፣ ከዝንጀሮ ጋር ፆታዊ ግንኙነት የሚፈፅሙ አስፈሪ ፍጡሮች፣ አውሬ ከመሆናቸው የተነሳ አናታቸው ላይ ቀንድ ያወጡ ናቸው ብሎ ያስተዋውቃቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ከሩዋንዳው አሻሽለው ጥላቻ ማሰራጨት ብቻ ሳይሆን 95% የኢትዮጵያ ህዝብ 5% የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እንዲነሳ ሲጠሩ ቆይተዋል፣ አሁንም ተግተው እየሰሩ ነው፡፡
 • የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመንግስት ሙሉ ተሳትፎና ድጋፍ ቱትሲ ላይ የተፈፀመ ነበር፡፡ ልክ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ሰራዊቱ፣ የኤርትራ ሰራዊት፣ የሶማሊያ ወታደሮች፣ መላው የኢትየጵያ ህዝብ፣ የክልሎች ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ ወዘተ አስተባብሮ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እንደዘመተው
 • የቱትሲ ሬሳዎች ወደ ወንዝ ይጣሉ ነበር፣ ገዳዮቻቸው ‹ወደ ኢትዮጵያ እየላክናችሁ ነው› እያሉ ሬሳ ላይ ያላግጡ ነበር – ቱትሲዎች ከኢትዮጵያ እንደሄዱ ነው የሚነገርላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮችም ማሕበረ ዴጎን ጨምሮ ትግራይ ሙሉ ንፁሃን እየገደሉ፣ ወደ ገደል እየወረወሩ ከሬሳ ጋር በኩራት ፎቶ እየተነሱ እንደሚጨፍሩት፡፡ የአማራ ሚሊሻዎች የሑሞራና ጠቅላላ የምዕራብ ኗሪ ተጋሩ ኩርንኩሪት አስረው፣ ገድለው በየቀኑ ከ150 በላይ ንፁሃን ከድልድይ ወደ ተከዘ ወንዝ እየወረወሩ እንደሚገኑ በአለማቀፍ ሚድያዎች እየተዘገበ የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡ ሬሳቸው በሱዳን በኩል እየተለቀመ ይገኛል፡፡
 • የሩዋንዳ ጨፍጫፊ መንግስት 581 ቶን ገጀራ አስመጥቶ እንደነበር ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም የትግራይ ጦርነት ሲጀመር አከባቢ 186,240 ገጀራ በአንድ የጉምሩክ ኮንተይነር ላይ ተይዟል፡፡ ሳይያዝ ገዳዮች እጅ ላይ የገባ አስቡት፡፡ እነዚህ ገጀራዎች በማይ ካድራ፣ ዳንሻ ወዘተ ፋኖዎች ንፁሃን ላይ ተጠቅመውባቸዋል፡፡ እነዚህ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የመንግስት ሚድያዎች ህዝቡ ያለውን መሳርያ ሁሉ ይዞ ወጥቶ ትግራዋይ እንዲጨፈጭፍ እያነሳሱ፣ ወጣት አዛውንቱ ገጀራና ሌላ መሳርያ ይዞ እየፎከረ በየቀኑ በቴሌቭዥን ማየት የተለመደ ሁኗል፡፡
 • ሁለቱም የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና ሌሎች የአለም ማህበረሰብ ድርጅቶች በዓይናቸው እያዩዋቸው ተከሰቱ፡፡ እንድያውም አንዳንድ አባል ሀገራት ገዳዮችን ሲደግፉ ታይተዋል፡፡
 • የሩዋንዳው ጄኖሳይድ በገንዘብ የደገፈ ፈሊሸር ካቡጋ የሚባል ነጋዴ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለጭፍጨፋው የሚያገለግሉ ገጀራዎች አስመጥቶ አከፋፍሏል፡፡ በኢትዮጵያም ለትግራይ ጄኖሳይድ የሚያገለግሉ ገጀራዎች እያስመጣ የሚያከፋፍለው የሑመራ ሰሊጥ ነጋዴው ወርቁ አይተነው የተባለ የአማራ ብሔርተኛ ነጋዴ ነው፡፡
 • ጄኖሳይድ ፈፃሚዎች በሁለቱም ኩነቶች አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳርያ ተጠቅመዋል፡፡ በሩዋንዳ ጄኖሳይድ በሦስት ወር ውስጥ ከ100,000-250,000 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው ይገመታል፡፡ በትግራይም በተመሳሳይ እስካሁን ከ 150,000 በላይ ሴቶች የጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ጦርነቱ ስላላለቀ ጥናት ባለመደረጉ ቁጥሩ ከዛ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
 • ቱትሲዎች #RPF (Rwandan Patriotic Front) የሚባል መድን ሰራዊት ነበራቸው፣ ልክ እንደ ትግራይ #TDF (Tigrai Defence Forces). RTF ልክ እንደ TDF በመንግስት ህዝቡ ላይ ስሙ በመጥፎ እንዲቀረፅ ተዘምቶበታል፡፡ ይሁን እንጂ የዘር ማጥፋት ዘመቻው ያቆመው RPF ነው – ልክ TDF እያደረገው እንዳለ፡፡

በጣም በብዙ መልኩ ይመሳሰላሉ፡፡

Share:

administrator

My life, my way.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *